እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አሮንን፦ ‘በትርህን በእጅህ ዘርጋ፤ የምድሩንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማልም በግብፅ ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ይወጣል።”
ዘፀአት 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ፤ ሙሴም በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አላቸው፤ “ከምድጃው ዕፍኝ ዐመድ ወስዳችሁ፣ ሙሴ በፈርዖን ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ፥ ሙሴም በፈርዖን ፊት ወደ ሰማያት ይበትነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “በእፍኛችሁ እየዘገናችሁ ከምድጃ ጥቂት ዐመድ ውሰዱ፤ እርሱንም ሙሴ በንጉሡ ፊት ወደ አየር ይበትነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ፤ ሙሴም በፈርዖን ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው። |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አሮንን፦ ‘በትርህን በእጅህ ዘርጋ፤ የምድሩንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማልም በግብፅ ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ይወጣል።”
እርሱም በግብፅ ሀገር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፤ በግብፅም ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ሻህኝ የሚያመጣ ቍስል ይሆናል” አላቸው።