ጠንቋዮችም ቍስል ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤ ቍስል ጠንቋዮችንና ግብፃውያንን ሁሉ ይዞአቸው ነበርና።
ዘፀአት 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አመዱን በፈርዖን ፊት ወስዶ ወደ ሰማይ በተነው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ሻህኝ የሚያወጣ ቍስል ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ከምድጃው ዐመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ ሰማይ በተነው፤ መግል የያዘ ዕባጭም በሰዎችና በእንስሳት ላይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድጃውም አመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ ሰማያት በተነው፥ በሰውና በእንስሳ ላይም ፈሳሽ የሚያወጣ ብጉንጅ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ጥቂት ዐመድ ከምድጃ ወስደው በንጉሡ ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ አየር በበተነው ጊዜ ሕዝቡና እንስሶቹ በብርቱ ቊስል ተመቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምድጃውም አመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ ሰማይ በተነው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ሻህኝ የሚያወጣ ቍስል ሆነ። |
ጠንቋዮችም ቍስል ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤ ቍስል ጠንቋዮችንና ግብፃውያንን ሁሉ ይዞአቸው ነበርና።
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ፤ ሙሴም በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው።
እርሱም በግብፅ ሀገር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፤ በግብፅም ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ሻህኝ የሚያመጣ ቍስል ይሆናል” አላቸው።