ዘፀአት 8:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ ሀገርህን ሁሉ በጓጕንቸሮች እመታለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱን ለመልቀቅ እንቢ ብትል አገርህን ሁሉ በጓጕንቸር መቅሠፍት እመታዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም በግብጽ ውኆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ እንቁራሪቶቹም ወጡ፥ የግብጽንም ምድር ሸፈኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እምቢ ብትል ግን ሀገርህን ለመቅጣት በጓጒንቸር እሸፍናታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ እኔ አገርህን ሁሉ በጓጕንቸሮች እመታለሁ፤ |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል፤ ወጥተውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህም፥ ወደ ሹሞችህም ቤት፥ በሕዝብህም ላይ፥ ወደ ቡሃቃዎችህም፥ ወደ ምድጃዎችህም ይገባሉ፤