ዘፀአት 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ሁሉ ስለ ገለባ እብቅ ሊሰበስቡ በግብፅ ምድር ሁሉ ተበተኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ሕዝቡ በጭድ ፈንታ ገለባ ለመሰብሰብ በግብጽ ምድር ሁሉ ተሰማሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ለገለባ የሚሆን እብቅ ሊሰበስቡ በግብጽ ምድር ሁሉ ተበተኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሕዝቡ ገለባ ፈልገው ለማግኘት በመላይቱ የግብጽ ምድር ተሰማሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ስለ ገለባ እብቅ ሊሰበስቡ በግብፅ ምድር ሁሉ ተበተኑ። |
እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃጠላሉ፤ ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኀይል አያድኑም፤ እንደ እሳትም ፍም ይሆኑብሻል፤ በላያቸውም ትቀመጫለሽ።
ስለዚህ ገለባ በእሳት ፍም እንደሚቃጠል፥ በነበልባልም እንደሚበላ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፤ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።
ድምፃቸውም በተራራ ላይ እንደ አሉ ሠረገሎች ድምፅ፥ ገለባውንም እንደሚበላ እንደ እሳት ነበልባል ድምፅ ነው፤ ለሰልፍም እንደ ተዘጋጀ እንደ ብዙና ብርቱ ሠራዊት ያኰበኵባሉ።
እግዚአብሔርም ተናግሮአልና የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍም ቤት ነበልባል፥ የዔሳውም ቤት ገለባ ይሆናሉ፤ እነርሱንም ያቃጥሉአቸዋል፤ ይበሉአቸውማል፤ ከዔሳውም ቤት ቅሬታ አይኖርም።