Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በዚህ መሠ​ረት ላይ በወ​ር​ቅና በብር፥ በከ​በረ ድን​ጋ​ይና በእ​ን​ጨት፥ በሣ​ርና በአ​ገዳ የሚ​ያ​ንጽ ቢኖ​ርም፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ማንም በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ወይም በብር፣ በከበረ ድንጋይ ወይም በዕንጨት፣ በሣር ወይም በአገዳ ቢያንጽ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ፥ በብር፥ በከበሩ ድንጋዮች፥ በእንጨት፥ በሣር፥ በገለባ ቢያንጽ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ፥ ወይም በብር በከበረ ድንጋይ፥ ወይም በእንጨት፥ በሣር ወይም በገለባ የሚገነባ ቢኖር

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 3:12
33 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ ገለባ እብቅ ሊሰ​በ​ስቡ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ተበ​ተኑ።


ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። ዕውቀትንም ገንዘብ ማድረግ ከብር ይሻላል።


ከብር ይልቅ ትምህርትን፥ ከተፈተነ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ።


በናስ ፋንታ ወር​ቅን፥ በብ​ረ​ትም ፋንታ ብርን፥ በእ​ን​ጨ​ትም ፋንታ ናስን፥ በድ​ን​ጋ​ይም ፋንታ ብረ​ትን እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ። ለአ​ለ​ቆ​ች​ሽም ሰላ​ምን፥ ለመ​ኳ​ን​ን​ት​ሽም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤


የሚ​ያ​ልም ነቢይ ሕል​ምን ይና​ገር፤ ቃሌም ያለ​በት ቃሌን በእ​ው​ነት ይና​ገር። ገለባ ከስ​ንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ወደ እነ​ርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ ጠማማ ትም​ህ​ር​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ይነ​ሣሉ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እና​ንተ የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን ትም​ህ​ርት የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትን፥ መለ​ያ​የ​ት​ንና ማሰ​ና​ከ​ያን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን እን​ድ​ታ​ው​ቁ​ባ​ቸው እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤


ነገር ግን ከተ​መ​ሠ​ረ​ተው በቀር ሌላ መሠ​ረት ሊመ​ሠ​ርት የሚ​ችል የለም፤ መሠ​ረ​ቱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።


የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሥራ ይገ​ለ​ጻል፤ እሳ​ትም በፈ​ተ​ነው ጊዜ ቀኑ ይገ​ል​ጠ​ዋል፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱ​ንም ሥራ እሳት ይፈ​ት​ነ​ዋል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በሌላ ቀላ​ቅ​ለው እን​ደ​ሚ​ሸ​ቅጡ እንደ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምና፤ በቅ​ን​ነት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተላከ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ና​ገ​ራ​ለን።


ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።


ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ።


እነዚህን አስተምርና ምከር። ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥


በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፤ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እያሳቱና እየሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።


ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።


ሌላ ልዩ ትም​ህ​ርት አታ​ምጡ፤ ልባ​ችሁ በመ​ብል ያይ​ደለ በጸጋ ቢጸና ይበ​ል​ጣ​ልና፤ በዚያ ይሄዱ የነ​በሩ እነ​ዚያ አል​ተ​ጠ​ቀ​ሙ​ምና።


ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።


ቅጥርዋም ከኢያሰጲድ የተሠራ ነበረ፤ ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች።


ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos