ዘፀአት 39:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሰ እንግድዓውን ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ፥ እንደ ልብሰ መትከፉ አሠራር ከወርቅና ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈትለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደረት ኪሱንም ጥበበኛ ባለሙያ እንደሚሠራው ሥራ በተመሳሳይ መንገድ ሠሩት፤ እንደ ኤፉዱም ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ በቀጭኑም ከተፈተለ በፍታ ሠሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደረቱን ኪስ ብልህ ሠራተኛ እንደሠራው እንደ ኤፉዱ አሠራር ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደረቱንም ኪስ ኤፉዱ ከተሠራባቸው ተመሳሳይ ነገሮች በተመሳሳይ የጥበብ ጥልፍ ሠሩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ የደረቱን ኪስ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ እንደ ኤፉዱ አሠራር ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረገው። |
“ለድንኳኑም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ዐሥር መጋረጆችን ሥራ፤ ኪሩቤልም በእነርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብልሃት ትሠራቸዋለህ።
የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ ልብሰ እንግድዓ፥ ልብሰ መትከፍ፥ ቀሚስም፥ ዥንጕርጕር እጀ ጠባብ፥ መጠምጠሚያ፥ መታጠቂያም፤ እነዚህንም በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ለወንድምህ ለአሮን፥ ለልጆቹም የተቀደሰ ልብስ ያድርጉ።