ዘፀአት 39:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወርቁንም ቀጥቅጠው እንደ ቅጠል ስስ አደረጉት፤ እንደ ፈትልም ቈረጡት። ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ ሰማያዊ፥ ሐምራዊም፥ ቀይ ግምጃም፥ የተፈተለም ጥሩ በፍታ፥ ከእርሱ ጠለፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበበኛ ባለሙያ እንደሚሠራው በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በቀጭን በፍታ ይሠራ ዘንድ ወርቁን በሥሡ ቀጥቅጠው እንደ ክር ቈራረጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወርቁንም ቀጥቅጠው እንደ ቅጠል ስስ አድርገው እንደ ፈትል ቆረጡት። ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራው በሰማያዊው፥ በሐምራዊው፥ በቀዩ ግምጃ፥ በተፈተለው ጥሩ በፍታ መካከል በእርሱ ጠለፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወርቁንም ቀጥቅጠው ስስ በማድረግ እንደ ክር አድርገው ቈራረጡት፤ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለም ጥሩ በፍታ ጋር በጥበብ አሠራር ጠለፉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወርቁንም ቀጥቅጠው እንደ ቅጠል ስስ አድርገው እንደ ፈትል ቈረጡ። ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ ሰማያዊ ሐምራዊም ቀይም ግምጃ የተፈተለም ጥሩ በፍታ ከእርሱ ጠለፉ። |
“ለድንኳኑም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ዐሥር መጋረጆችን ሥራ፤ ኪሩቤልም በእነርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብልሃት ትሠራቸዋለህ።
በእነርሱም ዘንድ ያሉት፥ ሥራ ሲሠሩ የነበሩት በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ ድንኳኑን ከዐሥር መጋረጃዎች ሠሩ፤ እነርሱንም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊም፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ሠሩ፤ በእነርሱም ላይ በጥልፍ ሥራ ኪሩቤልን አደረጉባቸው።