La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 37:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰባ​ቱ​ንም መብ​ራ​ቶ​ች​ዋን መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የመቅረዙን ሰባት መብራቶች፣ እንዲሁም መኰስተሪያዎችንና የኵስታሪ ማስቀመጫዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰባቱን መብራቶቹን፥ መኰስተሪያዎቹንና የኩስታሪ ማድረጊያዎቹን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለመቅረዙም ሰባት መብራቶችን፥ መኰስተሪያዎችንና የኲስታሪ ማኖሪያዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰባቱንም መብራቶች መኰስተሪያዎቹንም፥ የኩስታሪ ማድረጊያዎቹንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 37:23
11 Referencias Cruzadas  

ሰባ​ቱ​ንም መብ​ራ​ቶች ሥራ፤ በፊቱ ያበሩ ዘንድ መብ​ራ​ቶ​ቹን ያቀ​ጣ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።


መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋን፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ አድ​ርግ።


ጕብ​ጕ​ቦ​ች​ዋና ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ ከእ​ርሱ ጋር አንድ ነበሩ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተ​ቀ​ረጸ ከጥሩ ወርቅ ተሠ​ርቶ ነበር።


መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከአ​ንድ መክ​ሊት ጥሩ ወርቅ አደ​ረገ።


እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፣ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፣ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።


“መብ​ራ​ቶ​ቹን ስታ​በራ ሰባቱ መብ​ራ​ቶች በመ​ቅ​ረዙ ፊት ያበ​ራሉ ብለህ ለአ​ሮን ንገ​ረው።”


የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፤


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።


ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፤ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።


ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።