ዘፀአት 36:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማይነቅዝ ዕንጨት በድንኳኑ በአንደኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎችን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም ከግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን ሠሩ፤ በማደሪያው ድንኳን በአንድ በኩል ላሉት ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን ሠሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግራር እንጨት መወርወሪያዎችን ሠራ፥ በማደሪያው በአንደኛው በኩል ላሉት ሳንቃዎች አምስት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሥራ አምስት መወርወሪያዎችንም ከግራር እንጨት ሠሩ፤ በዚህ ዐይነት አምስቱ ከድንኳኑ በአንድ በኩል ላሉት ተራዳዎች ሲሆኑ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግራርም እንጨት በማደሪያው በአንደኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች፥ |
በድንኳኑም በሁለተኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎችን፥ ከድንኳኑም በስተኋላ በምዕራቡ ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎችን አደረጉ።