La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 32:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሌ​ዊም ልጆች ሙሴ እን​ዳለ አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም ቀን ከሕ​ዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሌዋውያኑ ሙሴ እንዳዘዛቸው ፈጸሙ፤ በዚያም ዕለት ከሕዝቡ ሦስት ሺሕ ያህል ዐለቁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሌዊም ልጆች ሙሴ እንዳለ አደረጉ፤ በዚያ ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሌዋውያንም ለቃሉ ታዛዦች በመሆን በዚያን ቀን ሦስት ሺህ ሰው ገደሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሌዊም ልጆች ሙሴ እንዳለ አደረጉ፤ በዚያም ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 32:28
12 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰይ​ፉን በወ​ገቡ ላይ ይታ​ጠቅ፤ ሂዱና በሰ​ፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ተመ​ላ​ለሱ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወን​ድ​ሙን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጎረ​ቤ​ቱን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የቅ​ር​ቡን ይግ​ደል” አላ​ቸው።


ሙሴም፥ “ዛሬ በረ​ከ​ትን እን​ዲ​ያ​ወ​ር​ድ​ላ​ችሁ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ከል​ጁና፥ ከወ​ን​ድሙ የተ​ነሣ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በእ​ጃ​ችሁ ደስ አሰ​ኛ​ች​ሁት” አላ​ቸው።


አሮን የሠ​ራ​ውን ጥጃ ስለ ሠሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ቀሠፈ።


በነ​ጋ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ “እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ገድ​ላ​ች​ኋል” ብለው በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ።


የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ባየው ጊዜ ከማ​ኅ​በሩ መካ​ከል ተነ​ሥቶ በእጁ ጦር አነሣ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች እን​ዲህ ስጡ፤ ከብ​ዙ​ዎቹ ብዙ፥ ከጥ​ቂ​ቶቹ ጥቂት ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ወረ​ሱት እንደ ርስ​ታ​ቸው መጠን ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሰ​ጣሉ።”


ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እንደ ሴሰኑ፥ በአ​ንድ ቀንም ሃያ ሦስት ሺህ ሰዎች እንደ ወደቁ አን​ሴ​ስን።


እና​ቱ​ንና አባ​ቱን አላ​የ​ኋ​ች​ሁም ላለ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ላላ​ወቀ፥ ልጆ​ቹ​ንም ላላ​ስ​ተ​ዋለ፤ ቃል​ህን ለጠ​በቀ፥ በቃል ኪዳ​ን​ህም ለተ​ማ​ጠነ።