ሰባት ቀን መሠዊያውን ታነጻዋለህ፤ ትቀድሰውማለህ፤ መሠዊያውም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሆናል፤ መሠዊያውንም የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።
ዘፀአት 30:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉንም ትቀድሳቸዋለህ፤ ቅዱሰ ቅዱሳንም ይሆናሉ፤ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅግ የተቀደሱ ይሆኑም ዘንድ ቀድሳቸው፤ የሚነካቸውም ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀድሳቸው ፍጹም የተቀደሱ ይሆናሉ፤ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት እነዚህን ሁሉ በመለየት ፍጹም የተቀደሱ ታደርጋቸዋለህ፤ እነርሱንም ፍጹም ቅዱሳን ስለ ሆኑ ሰውም ሆነ ሌላ ነገር ቢነካቸው ቅሥፈት ይደርስበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉንም ትቀድሳቸዋለህ፥ ቅድስተ ቅዱሳንም ይሆናሉ፤ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል። |
ሰባት ቀን መሠዊያውን ታነጻዋለህ፤ ትቀድሰውማለህ፤ መሠዊያውም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሆናል፤ መሠዊያውንም የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።
ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያና ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም ትቀባበታለህ።
ለሚቃጠል መሥዋዕትም የሚሆነውን መሠዊያ፥ ዕቃውንም ሁሉ ትቀባዋለህ፤ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሆናል።
ከካህናት ወገን ወንድ ሁሉ ይበላዋል፤ በዘመናችሁ ለዘለዓለም ሕግ ነው። ከሚቃጠለው የእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።”
ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ፤ ድንኳኒቱንና ዕቃዋን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው።
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ድንኳኑን ፈጽሞ በተከለባት፥ እርስዋንና ዕቃዋን ሁሉ በቀባና በቀደሰባት፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ በቀባና በቀደሰባት ቀን፥