La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 21:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሬ​ውም ትና​ን​ትና ከት​ና​ንት ወዲያ ተዋጊ መሆኑ ቢታ​ወቅ ለባ​ለ​ቤ​ቱም ቢመ​ሰ​ክ​ሩ​ለት፥ ባለ​ቤ​ቱም ባያ​ስ​ወ​ግ​ደው በሬ​ውን በበ​ሬው ፋንታ ይስጥ፤ የሞ​ተ​ውም ለእ​ርሱ ይሁ​ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሆኖም በሬው የመዋጋት ዐመል ያለው መሆኑ ከታወቀ፣ ባለቤቱም በረት ሳይዘጋበት ቢቀር፣ ባለቤቱ በሬውን በበሬው ፈንታ ይክፈል፤ የሞተውም እንስሳ ለርሱ ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሬው አስቀድሞ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ፥ ባለቤቱም ባይጠብቀው፥ በሬውን በበሬው ፈንታ ይስጥ፥ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን በሬው ተዋጊ መሆኑ ታውቆ ሳለ ባለቤቱ በበረት ውስጥ ሳይዘው ቀርቶ ከሆነ፥ በሬው ለሞተበት ሰው አንድ በሕይወት ያለ በሬ ካሣ ይክፈል፤ የሞተውንም በሬ ለራሱ ያስቀር።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሬውም አስቀድሞ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ፥ ባለቤቱም ባይጠብቀው፥ በሬውን በበሬው ፈንታ ይስጥ፥ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 21:36
4 Referencias Cruzadas  

በሬው ግን ከት​ና​ን​ትና ከት​ና​ንት ወዲያ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎ​ችም ለባ​ለ​ቤቱ ቢመ​ሰ​ክ​ሩ​ለት ባያ​ስ​ወ​ግ​ደ​ውም፥ ወን​ድን ወይም ሴትን ቢገ​ድል፥ በሬው ይወ​ገር፤ ባለ​ቤቱ ደግሞ ይገ​ደል።


“የሰው በሬ የሌ​ላ​ውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞ​ትም፥ ደኅ​ና​ውን በሬ ይሽጡ፤ ዋጋ​ው​ንም በት​ክ​ክል ይካ​ፈሉ፤ የሞ​ተ​ው​ንም ደግሞ በት​ክ​ክል ይካ​ፈሉ።


“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰ​ርቅ፥ ቢያ​ር​ደው ወይም ቢሸ​ጠው፥ በአ​ንድ በሬ ፋንታ አም​ስት በሬ​ዎች፥ በአ​ንድ በግም ፋንታ አራት በጎች ይክ​ፈል።


እን​ስ​ሳ​ንም ቢገ​ድል በነ​ፍስ ፋንታ ነፍስ ይክ​ፈል።