ለእኔም ለአገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ በሜዳም ተጣሉ፤ የሚገላግላቸውም አልነበረም፤ አንዱም ሌላውን መትቶ ገደለው።
ዘፀአት 21:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሁለት ሰዎችም እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ አንዱም ሌላውን በድንጋይ ወይም በጡጫ ቢመታ፥ ያም ባይሞት ነገር ግን በአልጋው ላይ ቢተኛ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰዎች ተጣልተው አንዱ ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታውና ተመቺው ሳይሞት በዐልጋ ላይ ቢውል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሰዎች ቢጣሉ፥ አንዱም ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታው፥ ባይሞት ነገር ግን በአልጋ ላይ ቢውል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሁለት ሰዎች ቢጣሉና አንደኛው ሌላውን በድንጋይ ቢፈነክተው ወይም በቡጢ ቢያቈስለው ካልገደለው በቀር በሞት አይቀጣ፤ የተመታው ሰው ታሞ በአልጋ ላይ ቢውል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ሰዎችም ቢጣሉ፥ አንዱም ሌላውን በድንጋይ ወይም በጡጫ ቢመታ፥ ያም ባይሞት ነገር ግን ታምሞ በአልጋው ላይ ቢተኛ፥ |
ለእኔም ለአገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ በሜዳም ተጣሉ፤ የሚገላግላቸውም አልነበረም፤ አንዱም ሌላውን መትቶ ገደለው።
በሁለተኛውም ቀን ወጣ፤ ሁለቱም የዕብራውያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፤ ሙሴም በዳዩን፥ “ለምን ባልንጀራህን ትመታዋለህ?” አለው።
“ከእስራኤል ልጆች አንዱን የሰረቀ ወይም ግፍ የፈጸመበት፥ ወይም አሳልፎ ቢሰጠው፥ ወይም በእርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ እርሱ ይገደል።
ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ሜዳ ቢወጣ፥ የመታው ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ተግባሩን ስላስፈታው ገንዘብ ይክፈለው፤ ለባለ መድኀኒትም ይክፈልለት።
“ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ ያረገዘችንም ሴት ቢያቈስሉ ተሥዕሎተ መልክእ ያልተፈጸመለት ፅንስም ቢያስወርዳት፥ የሴቲቱ ባል የጣለበትን ያህል ካሳ ይክፈል፤
“ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ የአንደኛውም ሰው ሚስት ባልዋን ከሚመታው ሰው እጅ ታድነው ዘንድ ብትቀርብ፥ እጅዋንም ዘርግታ ሁለቱን የብልቱን ፍሬዎች ብትይዝ፥