ዘፀአት 20:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴንም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ተናገር፤ ነገር ግን እንዳንሞት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አይናገር” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴን፣ “አንተ ራስህ ተናገረን፤ እኛም እናደምጥሃለን፤ እግዚአብሔር እንዲናገረን አታድርግ፤ አለዚያ መሞታችን ነው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን፤ ነገር ግን እንዳንሞት እግዚአብሔር አይናገረን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ሙሴን “አንተ ተናገረን፤ እናዳምጥሃለን፤ እግዚአብሔር ቢናገረን ግን እንሞታለን ብለን እንፈራለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴንም፦ አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን፤ እንዳንሞት ግን እግዚአብሔር አይናገረን አሉት። |
በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
በምድረ በዳ በማኅበሩ መካከል የነበረ እርሱ ነው፤ በደብረ ሲና ከአነጋገረው መልአክና፤ ከአባቶቻችንም ጋር ለእኛ ሊሰጠን የሕይወትን ቃል የተቀበለ እርሱ ነው።
ታዲያ ኦሪት ለምን ተሠራች? ኦሪትስ ኀጢአትን ታበዛት ዘንድ፥ ተስፋ ያደረገለት ያ ዘር እስኪመጣ ድረስ፥ በመላእክት በኩል በመካከለኛው እጅ ወረደች።
አምላካችሁን እግዚአብሔርን በኮሬብ በተሰበሰባችሁበት ቀን፦ ‘እንዳንሞት የአምላካችን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ አንስማ፤ ይህችን ታላቅ እሳት ደግሞ አንይ’ ብላችሁ እንደ ለመናችሁት ሁሉ።
እኔ የእግዚአብሔርን ቃል እነግራችሁ ዘንድ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር፤ እናንተ ከእሳቱ ፊት ፈርታችኋልና፥ ወደ ተራራው አልወጣችሁምና። እርሱም አለ፦
ወደ መለከት ድምፅም፥ ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፥ ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ።