ዘፀአት 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኅቱም ምን እንደሚደርስበት ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትጐበኘው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕፃኑም እኅት የሚደርስበትን ነገር ለማወቅ ራቅ ብላ ቆማ ታይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኅቱም ምን እንደሚደርስበት ለማየት በሩቅ ቆማ ትከታተለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕፃኑም እኅት የሚደርስበትን ነገር ለማየት ራቅ ብላ ትጠባበቀው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኅቱም የሚደርስበትን ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትመለከት ነበር። |
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፤ ተቀበረችም።
የቆሬ ወገን፥ የቀዓት ወገን። ቀዓትም እንበረምን ወለደ። በግብፅ ሀገር እነዚህን ሌዋውያንን የወለደቻቸው የሌዊ ልጅ የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።