ዘፀአት 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ይጠብቁ ነበር፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ሊያጠጡ የውኃዉን ገንዳ ሞሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ውሃው ጕድጓድ መጥተው የአባታቸውን በጎች ውሃ ለማጠጣት ገንዳውን ሞሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፥ የአባታቸውንም በጎች ሊያጠጡ የውሀውን ገንዳ ሞሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ውሃ ለመቅዳትና በገንዳ እየሞሉ የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማጠጣት ወደዚያ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም በጎች ሊያጠጡ የውኃውንም ገንዳ ሞሉ። |
በተመለከተም ጊዜ በሜዳው እነሆ ጕድጓድን አየ፤ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፤ ከዚያች ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓድዋም አፍ ታላቅ ድንጋይ ነበረች።
ፈርዖንም የዮሴፍን ስም “እስፍንቶፎኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ የምትሆን አስኔትንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።
የምድያም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እስራኤልን ከግብፅ እንደ አወጣ ሰማ።
የሙሴ አማት ዮቶርም የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እንጀራ ሊበሉ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ።
ሙሴም የአማቱን የምድያምን ካህን የዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ በጎቹንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።