La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ከኤ​ሎም ተጓዙ፤ ከግ​ብፅ ሀገር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በኤ​ሎ​ምና በሲና መካ​ከል ወዳ​ለ​ችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ከኤሊም ተነሥተው በኤሊምና በሲና መካከል ወደምትገኘው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከኤሊምም ተነሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር፥ በዓሥራ አምስተኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር፥ በዐሥራ አምስተኛው ቀን፥ ከኤሊም ተነሥተው በሲና እና በኤሊም መካከል ወዳለው “ሲን” ተብሎ ወደሚጠራው ምድረ በዳ መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከኤሊምም ተጓዙ፥ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከግብፅ አገር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 16:1
7 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።


በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት።


እነ​ር​ሱም ወደ ኤሎም መጡ፤ በዚ​ያም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምን​ጮ​ችና ሰባ የዘ​ን​ባባ ዛፎች ነበ​ሩ​ባት፤ በዚ​ያም በው​ኃው አጠ​ገብ ሰፈሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራ​ፊ​ድም ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።