“ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤታችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ።
ዘፀአት 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በእናንተም ዘንድ እርሾ ያለበት እንጀራ አይታይ፤ በአውራጃዎቻችሁ ሁሉ እርሾ አይኑር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነዚህም ሦስት ቀናት ቂጣ ትበላላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ እርሾ ያለበት ነገር ፈጽሞ አይገኝ፤ በምድራችሁም አዋሳኝ በየትኛውም ቦታ እርሾ ፈጽሞ አይኑር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀንም ሙሉ ያልቦካ ቂጣ ትበላለህ፥ በአንተም ዘንድ እርሾ ያለበት አይታይ፥ በድንበርህም ሁሉ እርሾ አይታይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ሰባት ቀን ድረስ ያልቦካ እንጀራ ትበላላችሁ፤ እርሾም ሆነ የቦካ እንጀራ ከቶ በምድራችሁ አይገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ እንጀራ ትበላለህ፤ በአንተም ዘንድ እርሾ ያለበት እንጀራ አይታይ፤ በድንበርህም ሁሉ እርሾ አይታይ። |
“ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤታችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ።
ሰባት ቀን በቤታችሁ እርሾ አይገኝ፤ እርሾ ያለበትንም እንጀራ የሚበላ ሁሉ ያ ሰው ከመጻተኛው ጀምሮ እስከ ሀገር ልጁ ድረስ፥ ከእስራኤል ማኅበር ተለይቶ ይጥፋ።
አሁንም በዓላችሁን አድርጉ፤ ነገር ግን እውነትና ንጽሕና ባለው እርሾ ነው እንጂ በአሮጌው እርሾ፥ በኀጢአትና በክፋት እርሾም አይደለም።