በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ልጆች በየቀኑ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ የቂጣውን በዓል በታላቅ ደስታ ሰባት ቀን አደረጉ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በዜማ ዕቃ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
ዘፀአት 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ ሰባተኛውም ቀን የእግዚአብሔር በዓል ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰባት ቀን ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር በዓል ታደርጋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላለህ፥ በሰባተኛውም ቀን ለጌታ በዓል ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ የሌለበት ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር ክብር በዓል ታደርጋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላለህ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር በዓል ይሆናል። |
በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ልጆች በየቀኑ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ የቂጣውን በዓል በታላቅ ደስታ ሰባት ቀን አደረጉ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በዜማ ዕቃ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
“የቂጣውን በዓል ትጠብቀዋለህ። በሚያዝያ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና በታዘዘው ዘመን በሚያዝያ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።
ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ሰባተኛዋ ቀን ቅድስት ጉባኤ ትሁንላችሁ፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩባት።”
ስድስት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ፤ ሰባተኛው ቀን ግን መውጫው ስለሆነ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በዓል ይሁን፤ ለነፍስም ከሚሠራው በቀር ሥራን ሁሉ አታድርግበት።