ዘፀአት 12:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሀገር ልጅ፥ በእናንተ መካከልም ለሚቀመጡ መጻተኞች አንድ ሥርዐት ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ሕግ በዜጋውም ሆነ በመካከላችሁ በሚኖሩት መጻተኞች ላይ እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአገሩ ተወላጅና በእናንተ መካከልም ለሚቀመጡ መጻተኞች አንድ ሥርዓት ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ይህ ሕግ ለእናንተ ለእስራኤላውያኑም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖሩት መጻተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ይፈጸም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአገር ልጅ በእናንተ መካከልም ለሚቀመጡ እንግዶች አንድ ሥርዓት ይሆናል።” |
እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና፤ ወደ እናንተ የመጣ እንግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁንላችሁ፤ እርሱን እንደ ራሳችሁ ውደዱት፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
ትውልዱ በእስራኤል ልጆች መካከል ቢሆን፥ ወይም በመካከላቸው የሚኖር መጻተኛ ቢሆን፥ ሳያውቅ ኀጢአትን ለሚሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆንለታል።
ባለማወቅ ነፍስ የገደለ ሁሉ ይሸሽባቸው ዘንድ እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች፥ በመካከላቸውም ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ።
ወደ አገራችሁ መጻተኛ ቢመጣ፥ የእግዚአብሔርን ፋሲካ እንደ ፋሲካው ሕግ እንደ ትእዛዙም ያድርግ፤ ለመጻተኛና ለሀገር ልጅ አንድ ሥርዐት ይሁንላችሁ።”
በዚህም አይሁዳዊ፥ ወይም አረማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ናችሁና።
በእርሱ ዘንድ አይሁዳዊ፥ ግሪካዊም፥ የተገዘረ፥ ያልተገዘረም፥ አረመኔም፥ ባላገርም፥ ቤተ ሰብእና አሳዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክርስቶስ ለሁሉ በሁሉም ዘንድ ነው።