ዘፀአት 12:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ሙሴ እንዳዘዘ አደረጉ። ከግብፃውያንም የብርንና የወርቅን ዕቃ፥ ልብስንም ተዋሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ሙሴ እንዳዘዛቸው የብርና የወርቅ ዕቃዎች፣ እንደዚሁም ልብስ እንዲሰጧቸው ግብጻውያኑን ጠየቋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች እንደ ሙሴ ቃል አደረጉ፥ ከግብፃውያንም የብርንና የወርቅን ዕቃ ልብስንም ለመኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ሙሴ እንዳዘዛቸውም አደረጉ፤ ይኸውም የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እንዲሁም ልብስ እንዲሰጡአቸው ግብጻውያንን ጠየቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ሙሴ እንዳዘዘ አደረጉ፤ ከግብፃውያንም የብርንና የወርቅን ዕቃ ልብስንም ለመኑ። |
በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በገንዘቦችና በእንስሶች፥ በሌላም ስጦታ ይረዷቸው ነበር።