እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ሀገር ላይ እጅህን ዘርጋ፤ አንበጣም በምድር ላይ ይወጣል፤ ከበረዶውም የተረፈውን የምድር ቡቃያ ሁሉና የዛፉን ፍሬ ሁሉ ይበላል።”
ዘፀአት 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድሩንም ፊት ይሸፍናል፤ ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም ተርፎ በምድር ላይ የቀረላችሁን ትርፍ ሁሉ ይበላል፤ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንበጣዎቹም ምድሪቱ እስከማትታይ ድረስ ይሸፍኗታል፤ በመስክህ ላይ እያቈጠቈጠ ያለውን ዛፍ ሁሉ ሳይቀር ከበረዶ የተረፈውንም ጥቂቱን ሁሉ ይበሉታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታል፥ ማንም ምድሩን ማየት አይችልም፤ ከበረዶውም ተርፎ የቀረላችሁን ሁሉ ይበሉታል፥ ያደገላችሁንም በሜዳ ያለ ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንበጣውም መንጋ እጅግ ብዙ ከመሆኑ የተነሣ ምድሪቱን በመላ ይሸፍናል፤ ከበረዶው የተረፈውን ነገር፥ ዛፉን ሁሉ ምንም ሳይቀር ይበላዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታልና ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም አምልጦ የተረፈላችሁን ትርፍ ይበሉታል፤ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፤ |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ሀገር ላይ እጅህን ዘርጋ፤ አንበጣም በምድር ላይ ይወጣል፤ ከበረዶውም የተረፈውን የምድር ቡቃያ ሁሉና የዛፉን ፍሬ ሁሉ ይበላል።”
የምድሩንም ፊት ፈጽሞ ሸፈነው፤ ሀገሪቱም ጠፋች፤ የሀገሪቱን ቡቃያ ሁሉ ከበረዶውም የተረፈውን፥ በዛፉ የነበረውን ፍሬ ሁሉ በላ፤ ለምለም ነገር በዛፎች ላይ፥ በእርሻውም ቡቃያ ሁሉ ላይ በግብፅ ሀገር ሁሉ አልቀረም።
እሳት በፊታቸው ትበላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፤ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋላቸውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእርሱም የሚያመልጥ የለም።