ዘፀአት 10:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የአንበጣውም መንጋ እጅግ ብዙ ከመሆኑ የተነሣ ምድሪቱን በመላ ይሸፍናል፤ ከበረዶው የተረፈውን ነገር፥ ዛፉን ሁሉ ምንም ሳይቀር ይበላዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 አንበጣዎቹም ምድሪቱ እስከማትታይ ድረስ ይሸፍኗታል፤ በመስክህ ላይ እያቈጠቈጠ ያለውን ዛፍ ሁሉ ሳይቀር ከበረዶ የተረፈውንም ጥቂቱን ሁሉ ይበሉታል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታል፥ ማንም ምድሩን ማየት አይችልም፤ ከበረዶውም ተርፎ የቀረላችሁን ሁሉ ይበሉታል፥ ያደገላችሁንም በሜዳ ያለ ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የምድሩንም ፊት ይሸፍናል፤ ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም ተርፎ በምድር ላይ የቀረላችሁን ትርፍ ሁሉ ይበላል፤ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታልና ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም አምልጦ የተረፈላችሁን ትርፍ ይበሉታል፤ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፤ Ver Capítulo |