እርሱም፥ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብቶቹ የሚሰበሰቡበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩአቸው” አላቸው።
ኤፌሶን 5:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ዘመን ክፉ ስለ ሆነ በማናቸውም አጋጣሚ ጊዜ ተጠቀሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። |
እርሱም፥ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብቶቹ የሚሰበሰቡበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩአቸው” አላቸው።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “ ገና ለጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው፤ በጨለማ የሚመላለስ የሚሄድበትን አያውቅምና ጨለማ እንዳያገኛችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤