ኤፌሶን 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁሉ ሙሉ የሚሆን ሁሉም ከእርሱ የተገኘ ከሁሉም በላይ ያለ የሁሉ አባት እግዚአብሔር አንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሁሉም በላይ የሆነ፣ በሁሉም የሚሠራ፣ በሁሉ የሚኖር የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሁሉ በላይ የሚሆን፥ በሁሉም የሚሠራ፥ በሁሉም የሚኖር፥ አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ፥ በሁሉም የሚሠራ፥ በሁሉም የሚኖር፥ የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። |
አንተ አባታችን ነህ፤ አብርሃም ግን አላወቀንም፤ እስራኤልም አልተገነዘበንም፤ ነገር ግን አንተ አባታችን አድነን፤ ስምህም ለዘለዓለም በእኛ ላይ ነው።
ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?
እነርሱም በግንባራቸው ወድቀው፥ “የነፍስና የሥጋ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንድ ሰው ኀጢአት ቢሠራ የእግዚአብሔር ቍጣ በማኅበሩ ላይ ይሆናልን?” አሉ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ አለው፥ “የሚወደኝ ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፤ ወደ እርሱም መጥተን በእርሱ ዘንድ ማደሪያ እናደርጋለን።
እኔን የወደድህበት ፍቅር በእነርሱ ይኖር ዘንድ፥ እኔም በእነርሱ እኖር ዘንድ ስምህን ነገርኋቸው፤ ደግሞም እነግራቸዋለሁ፤”
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞች ሂጂና፦ ወደ አባቴ፥ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ፥ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው” አላት።
ለእኛስ ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ እኛም በእርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አለን።
የእግዚአብሔርን ታቦትስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው? የሕያው እግዚአብሔር ማደሪያዎች እኛ አይደለንምን? እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “እኔ በእነርሱ አድራለሁ፤ በመካከላቸውም እኖራለሁ፤ አምላካቸውም እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል።”
ከመላእክት ሁሉ በላይ ከመኳንንትና ከኀይላት፥ ከአጋእዝትና ከሚጠራውም ስም ሁሉ በላይ፥ በዚህ ዓለም ብቻ አይደለም፤ በሚመጣውም ዓለም እንጂ።
ከአባታችን ከእግዚአብሔር አብ፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ከእምነት ጋር ሰላምና ፍቅር ለወንድሞቻችን ይሁን።