ብዙዎች አሕዛብ እርሱን ያደንቃሉ፤ ነገሥታትም አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያውቁታልና፥ ያልሰሙትም ያስተውሉታልና።
ኤፌሶን 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌላ ዘመን ለሰው ልጆች ያልተገለጠ ዛሬ ለቅዱሳን ሐዋርያቱና ለነቢያቱ በመንፈስ ቅዱስ እንደ ተገለጠ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ምስጢር በመንፈስ አሁን ለቅዱሳኑ ሐዋርያትና ነቢያት የተገለጠውን ያህል ባለፉት ዘመናት ለነበሩ ሰዎች አልተገለጠም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ምስጢር አሁን ለቅዱሳኑ ሐዋሪያትና ለነቢያት በመንፈስ እንደተገለጠው ባለፉት ትውልዶች ለነበሩ አልተገለጠም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ምሥጢር በእግዚአብሔር መንፈስ ለቅዱሳን ሐዋርያቱና ነቢያቱ አሁን እንደተገለጠው ዐይነት ባለፉት ዘመናት ለነበሩት ሰዎች አልተገለጠም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም መስበክ በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነ የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ፥ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለነቢያት በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች አልታወቀም። |
ብዙዎች አሕዛብ እርሱን ያደንቃሉ፤ ነገሥታትም አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያውቁታልና፥ ያልሰሙትም ያስተውሉታልና።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤
ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ተመኙ፤ አላዩምም፤ እናንተ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኙ፥ አልሰሙም።”
ስለዚህ የእግዚአብሔር ጥበቡ እንዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም።
ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል።
ያ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ እርሱ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፥ “ለአይሁዳዊ ሰው ሄዶ ከባዕድ ወገን ጋር መቀላቀል እንደማይገባው ታውቃላችሁ፤ ለእኔ ግን ከሰው ማንንም ቢሆን እንዳልጸየፍና ርኩስ ነው እንዳልል እግዚአብሔር አሳየኝ።
ይህም በነቢያት ቃልና የዘለዓለም ገዥ በሚሆን በእግዚአብሔር ትእዛዝ በዚህ ወራት ተገለጠ፤ አሕዛብ ሁሉ ይህን ሰምተውና ዐውቀው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ።