La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤፌሶን 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ እና​ንተ ከቅ​ዱ​ሳን ጋር ባላ​ገ​ሮ​ችና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ሰቦች እንጂ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚህ የተነሣ እናንተ ከቅዱሳን ጋራ የአንድ አገር ዜጋ፣ የእግዚአብሔርም ቤተ ሰብ አባል ናችሁ እንጂ፣ ከእንግዲህ ወዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ዜጎችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ ባዕዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር የአንድ አገር ዜጎችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።

Ver Capítulo



ኤፌሶን 2:19
14 Referencias Cruzadas  

ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!


እን​ግ​ዲህ ጊዜ ሳለን ለሁሉ መል​ካም ሥራ እና​ድ​ርግ፤ ይል​ቁ​ንም ለሃ​ይ​ማ​ኖት ሰዎች።


ያን​ጊዜ ክር​ስ​ቶ​ስን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕግ የተ​ለ​ያ​ችሁ ነበ​ራ​ችሁ፤ ከተ​ስ​ፋው ሥር​ዐ​ትም እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ችሁ፤ ተስ​ፋም አል​ነ​በ​ራ​ች​ሁም፤ በዚ​ህም ዓለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር።


በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያሉ ነገ​ዶች ሁሉ ለሚ​ጠ​ሩት ለእ​ርሱ፤


አሕ​ዛ​ብን ወራ​ሾ​ቹና አካሉ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ፥ በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነው ተስፋ አንድ ይሆኑ ዘንድ።


እኛስ ሀገ​ራ​ችን በሰ​ማይ ያለ​ችው ናት፤ ከዚ​ያም እር​ሱን ጌታ​ችን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ጠ​ባ​በ​ቃ​ለን።


እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።


በዚህ የሚ​ኖር ከተማ ያለን አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​መ​ጣ​ውን እን​ሻ​ለን እንጂ።


ወዳጆች ሆይ! ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤


የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።