መክብብ 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከድስት በታች እንደሚቃጠል እሾህ ድምፅ የሰነፍ ሣቅ እንዲሁ ነው፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞኞች ሣቅ፣ ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ የእሾኽ ማገዶ ነው፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከድስት በታች እንደሚቀጣጠል እሾህ ድምፅ የአላዋቂ ሳቅ እንዲሁ ነው፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞኝ ሳቅ ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ እሾኽ ስለ ሆነ ትርጒም የሌለው ከንቱ ነገር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከድስት በታች እንደሚቃጠል እሾህ ድምፅ የሰነፍ ሳቅ እንዲሁ ነው፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። |
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።
አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ተድላና ደስታ እንዳደረግህ፥ አልዓዛርም እንዲሁ ሁልጊዜ በችጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እንዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድላና ደስታ ያደርጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀበላለህ።
ዛሬ ለምትጠግቡ፥ ወዮላችሁ፥ ትራባላችሁና፤ ዛሬ ለምትስቁም ወዮላችሁ፥ ታዝናላችሁና፤ ታለቅሳላችሁምና።