መክብብ 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ድካም ሁሉ በአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው ጥረት ሁሉ ለአፉ ነው፤ ፍላጎቱ ግን ፈጽሞ አይረካም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ድካም ሁሉ ለአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው በሥራ መድከሙ የሚበላውን ነገር ለማግኘት ነበር፤ ይሁን እንጂ “በቃኝ!” ማለት አያውቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ድካም ሁሉ ለአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም። |
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ ብዙ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም ብዙ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፥ “ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል” አልሁ።
“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
ሰውነቴንም እንዲህ እላታለሁ፦ ሰውነቴ ሆይ፥ የሰበሰብሁልሽ ለብዙ ዓመታት የሚበቃሽ የደለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበልሽ።
የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”