መክብብ 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ደዌ አለ፤ ለመከራው በባለቤቱ ዘንድ የተቈጠበች ባለጠግነት ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፀሓይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፦ ይህም ለባለቤቱ ጕዳት የተከማቸ ሀብት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያችም ሀብት በክፉ ነገር ትጠፋለች፥ ልጅንም ቢወልድ በእጁ ምንም የለውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዓለም እጅግ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ደግሞ አየሁ፤ ይኸውም ሰዎች ለክፉ ቀን ይጠቅመናል ብለው ሀብት ያከማቻሉ፤ ነገር ግን በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ሀብታቸውን ያጡና ለልጆቻቸው የሚተላለፍ ምንም ነገር ሳይተርፋቸው ይቀራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፀሐይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፥ ለመከራው በባለቤቱ ዘንድ የተቈጠበች ባለጠግነት ናት። |
ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።
አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ? ሰውነቴንስ ከደስታ ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።
ይህን ሁሉ በአንድነት አየሁ፥ ከፀሓይም በታች ወደ ተደረገው ሥራ ሁሉ ልቤን ሰጠሁ፤ ሰውም ሰውን ለመጕዳት ገዥ የሚሆንበት ጊዜ አለ።
በዚያም ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል።
በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፣ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።
ዘኬዎስም ቆመና ጌታችንን እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገንዘቤን እኩሌታ ለነዳያን እሰጣለሁ፤ የበደልሁትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከፍለዋለሁ።”