መክብብ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔም አስቀድመው በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ከበርሁ፥ ታላቅም ሆንሁ። ጥበቤም ከእኔ ጋር ጸናችልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ እጅግ ታላቅ ሆንሁ፤ በዚህ ሁሉ ጥበቤ ከእኔ ጋራ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቅም ሆንሁ፥ ከእኔም አስቀድመው በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ከበርሁ፥ ደግምም ጥበቤ ከእኔ ጋር ጸናች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ የከበርኩ ታላቅ ሰው ሆንኩ፤ ጥበቤም ከእኔ ጋር ጸንታ ኖረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቅም ሆንሁ፥ ከእኔም አስቀድመው በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ከበርሁ፥ ደግምም ጥበቤ ከእኔ ጋር ጸንታ ቀረች። |
እኔም መጥቼ በዐይኔ እስካይ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም ነበር ፤ እነሆም፥ እኩሌታውን አልነገሩኝም ነበር፤ በሀገሬ ሳለሁ ከነገሩኝ ይልቅ የበለጠ መልካም ተጨማሪ አየሁ።
እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
እግዚአብሔርም ሰሎሞንን በእስራኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገነነው፤ ከእርሱ በፊትም ለነበሩት ነገሥታት ያልሆነውን የመንግሥት ክብር ሰጠው።
የዳዊት ልጅ ሰሎሞንም በመንግሥቱ በረታ፤ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ፤ እጅግም አከበረው፤ አገነነውም።
እኔ በልቤ፥ “እነሆ፥ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ላይ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ጥበብን አበዛሁ፤ ልቤንም ለጥበብና ለዕውቀት ሰጠሁ፥” በማለት ተናገርሁ።