መክብብ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌም ለእስራኤል የነገሠ የዳዊት ልጅ የሰባኪው የሰሎሞን ቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም የነገሠው፣ የዳዊት ልጅ፣ የሰባኪው ቃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌም የነገሠ የሰባኪው የዳዊት ልጅ ቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሩሳሌም ነግሦ የነበረ ጥበበኛው የዳዊት ልጅ የተናገረው የጥበብ ቃል ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌም የነገሠ የሰባኪው የዳዊት ልጅ ቃል። |
ደግሞም፦ ንጉሥ በይሁዳ አለ ብለው ስለ አንተ በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ ነቢያትን አቁመሃል፤ አሁንም ለንጉሡ ይህን ቃል ያወሩለታል፤ እንግዲህ መጥተህ በአንድነት እንማከር።”
እነሆ፥ ይህን ነገር አገኘሁ ይላል ሰባኪው፥ መደምደሚያን ለማግኘት አንዲቱን በአንዲቱ ጨምሬ ወደ ነገሩ ሁሉ መደምደሚያ እደርስ ዘንድ ብመረምር፥
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
“ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የነገርሁህንም የመጀመሪያውን ስብከት ስበክላት” አለው።