አህያይቱን በወይን ግንድ ያስራል፤ የአህያይቱንም ግልገል በወይን ሐረግ፤ ልብሱን በወይን ያጥባል፤ መጐናጸፊያውንም በዘለላው ደም።
ዘዳግም 8:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካምና ሰፊ ምድር፥ ከሜዳና ከተራሮች የሚመነጩ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾችም ወዳሉባት ምድር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ጅረቶችና የኵሬ ውሃ ወዳለበት፣ ምንጮች ከየሸለቆውና ከየኰረብታው ወደሚፈስሱበት ወደ መልካሚቱ ምድር ያገባሃል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላክህ ወደ መልካም ምድር፥ ከሸለቆና ከኮረብታ የሚመነጩ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾች፥ ምንጮችም ወዳሉባት ምድር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካሚቱ ለምለም ምድር ሊያስገባህ አምጥቶሃል፤ ያቺም ምድር ከሸለቆዎችና ከኮረብቶች የሚመነጩ ወንዞችና ጅረቶች፥ ፈሳሾች ምንጮችም ይገኙበታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካም ምድር፥ ከሸለቆና ከኮረብታ የሚመነጩ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾች ምንጮችም ወዳሉባት ምድር፥ |
አህያይቱን በወይን ግንድ ያስራል፤ የአህያይቱንም ግልገል በወይን ሐረግ፤ ልብሱን በወይን ያጥባል፤ መጐናጸፊያውንም በዘለላው ደም።
ይህም መጥቼ ምድራችሁን ወደምትመስለው ምድር፥ እህልና የወይን ጠጅ፥ እንጀራና ወይን፥ ወይራና ማር ወዳለባት ምድር እስካፈልሳችሁ ድረስ በሕይወት እንድትኖሩ፥ እንዳትሞቱም ነው። ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር ያድናችኋል ብሎ ያታልላችኋልና አትስሙት።
ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም ሀገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊዪቱና ወደ መልካሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
ይህም መጥቼ ምድራችሁን ወደምትመስለው ምድር፥ እህልና የወይን ጠጅ፥ እንጀራና ወይን ወዳለባት ምድር እስካፈልሳችሁ ድረስ ነው።
አሁን የወይኔን ቦታ በተመለከተ የወዳጄን መዝሙር ለወዳጄ እዘምራለሁ። ለወዳጄ በፍሬያማው ቦታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው።
ፍሬዋንና በረከቷንም ትበሉ ዘንድ ወደ ቀርሜሎስ አገባኋችሁ፤ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ።
በዚያ ቀን ከግብፅ ምድር ወዳዘጋጀሁላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ ከምድር ሁሉ ወደምትበልጥ ምድር አወጣቸው ዘንድ እጄን አነሣሁ።
በሄዳችሁም ጊዜ ተዘልለው ወደ ተቀመጡ ሕዝብ ትደርሳላችሁ፤ ምድሪቱም ሰፊ ናት፤ እግዚአብሔርም በምድር ካለው ነገር ሁሉ አንዳች የማይጐድልባትን ስፍራ በእጃችሁ ሰጥቶአል” አሉ።