ዘዳግም 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን፥ ሥርዐቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዛሬዪቱ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሕጉንና ሥርዐቱን ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዛሬ እኔ አንተን የማዘውን ትእዛዞቹንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ፥ ጌታ አምላክህን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህን በመርሳት፥ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች፥ ደንቦችና ሥርዓቶች እንዳታፈርስ ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤ |
አንቺ ግን ሰማያትን የፈጠረውን፥ ምድርንም የመሠረታትን ፈጣሪሽን እግዚአብሔርን ረስተሻል፤ ያጠፋሽ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሻል፤ ይቈጣሽ ዘንድ መክሮአልና፤ አሁን የሚያስጨንቅሽ ቍጣው የት አለ?
አባቶቻቸው ስለ በዓል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያንዳንዱ ለባልንጀራው በሚናገራት ሕልማቸው ሕዝቤን ስሜን ለማስረሳት ያስባሉ።
እርሱም በዘርፉ ይሁንላችሁ፤ ትመለከቱታላችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ታስባላችሁ፤ ታደርጉአቸውማላችሁ፤ እነርሱን በመከተል ያመነዘራችሁባትን የሕሊናችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ አትከተሉ።
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
እነሆ፥ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዐትና ፍርድን አሳየኋችሁ።
“ለራስህ ዕወቅ፤ ሰውነትህን ፈጽመህ ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ይህን ሁሉ ነገር አትርሳ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ከልቡናህ አይውጣ፤ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህም አስተምራቸው።
ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልማስሃቸውንም የተማሱ ጕድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም ወይንና ወይራ በሰጠህ ጊዜ፥ በበላህና በጠገብህም ጊዜ፤
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረጉ፤ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በዓሊምንና አስታሮትን አመለኩ።