ዘዳግም 32:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በክርክር ውኃ ለቃሌ አልታዘዛችሁምና፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል አልቀደሳችሁኝምና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ፣ በቃዴስ መሪባ ውሃ አጠገብ በእኔ ላይ መታመናችሁን በእስራኤላውያን ፊት ስላጐደላችሁና ቅድስናዬንም በእስራኤላውያን መካከል ስላላከበራችሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ፥ በቃዴስ በመሪባ ውሃ አጠገብ በእኔ ላይ መታመናችሁን በእስራኤላውያን ፊት ስላጐደላችሁና ቅድስናዬንም በእስራኤላውያን መካከል ስላላከበራችሁ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ሁለታችሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ለእኔ ታማኞች ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ከተማ አጠገብ በምትገኘው በመሪባ ውሃ ምንጮች አጠገብ በነበራችሁበት ጊዜ በእስራኤል ሕዝብ ፊት እንድከበር አላደረጋችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውኃ ስለ በደላችሁኝ፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል ስላልቀደሳችሁኝ፥ |
የደቡቡም ድንበር ከታማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብፅ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ይሆናል። የደቡቡም ድንበር ይህ ነው።
ሙሴም አሮንን፥ “እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እመሰገናለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ደነገጠ።
እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አላከበራችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የክርክር ውኃ ነው።”
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?