ከሞቱት ደምና ከኀያላን ስብ፥ የዮናታን ቀስት ባዶዋን አልተመለሰችም፤ የሳኦልም ሰይፍ ባዶዋን አልተመለሰችም።
ዘዳግም 32:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተወጉት፥ ከተማረኩትም ደም፥ ፍላጻዎቼን በደም አሰክራለሁ፤ ከጠላት አለቆችም ራስ ሰይፌ ሥጋን ትበላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰይፌ ሥጋ በሚበላበት ጊዜ፣ ፍላጾቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ደሙ የታረዱትና የምርኮኞች፣ የጠላት አለቆችም ራስ ደም ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተገደሉት ደም፥ ከተማረኩትም ደም፥ ከጠላት አለቆችም ራስ፥ ፍላጾቼን በደም አሰክራለሁ፥ ሰይፌም ሥጋ ይቆራርጣል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተገደሉትና ከተማረኩት ከጠላት መሪዎችም ራስ ደም ፍላጻዎቼን አሰክራለሁ፤ ሰይፌ የጠላትን ሥጋ ይቈራርጣል።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተወጉት ከተማረኩትም ደም፥ 2 ፍላጾቼን በደም አሰክራለሁ፤ 2 ከጠላት አለቆችም ራስ 2 ሰይፌ ሥጋ ይበላል። |
ከሞቱት ደምና ከኀያላን ስብ፥ የዮናታን ቀስት ባዶዋን አልተመለሰችም፤ የሳኦልም ሰይፍ ባዶዋን አልተመለሰችም።
ወራዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥተዋል፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።
“ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገርን ስለ ምን እግዚአብሔር ተናገረብን? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ኀጢአት ምንድን ነው? ቢሉህ፥
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ ቅጣት አቍስዬሃለሁና።
ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የአምላካችን የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ በልቶ ይጠግባል፤ በደማቸውም ይሰክራል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መሥዋዕት በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ነውና።
“በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶልም አውሩ፤ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ።
ሄ። እግዚአብሔር እንደ ጠላት ሆነብኝ፤ እስራኤልን አሰጠመ። አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፤ አንባዎችዋንም አጠፋ። በይሁዳም ሴት ልጅ ውርደትንና ጕስቍልናን አበዛ።