ዘዳግም 32:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ ሐረጋቸውም ከገሞራ ነው፤ ፍሬአቸውም ሐሞት ነው፤ ዘለላቸውም መራራ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይናቸው ከሰዶም ወይን፣ ከገሞራም ዕርሻ ይመጣል፤ የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፣ ዘለላቸውም በምሬት የተሞላ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤ ፍሬያቸው በመርዝ የተሞላ፥ ዘለላቸውም መራራ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችን እንደ ሰዶምና ገሞራ የረከሱ ናቸው፤ እነርሱም መራራና መርዘኛ ፍሬ እንደሚሰጥ የወይን ተክል ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ 2 ከገሞራም እርሻ ነው፤ 2 ፍሬያቸው ሐሞት ነው፤ 2 ዘለላውም መራራ ነው። |
እናንተ የሰዶም አለቆች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ።
ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድን ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ጠበቅሁት፤ ነገር ግን እሾህን አፈራ።
እኔ የተመረጠች ወይን፥ ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንዴት መራራ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?
በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
ሄዶ የእነዚያን አሕዛብ አማልክት ያመልክ ዘንድ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ልቡን ዛሬ የሚያስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይኑርባችሁ፤ ሐሞትና እሬትም የሚያበቅል ሥር አይሁንባችሁ።
አስተውሉ፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ የሚያቃልል አይኑር፤ ሕማምን የምታመጣ፥ ብዙዎችንም የምታስታቸውና የምታረክሳቸው መራራ ሥር የምትገኝበትም አይኑር።