Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሰቈቃወ 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ዋው። የማ​ንም እጅ ሳይ​ወ​ድ​ቅ​ባት ድን​ገት ከተ​ገ​ለ​በ​ጠች፥ ከሰ​ዶም ኀጢ​አት ይልቅ የወ​ገኔ ሴት ልጅ ኀጢ​አት በዛች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በሕዝቤ ላይ የደረሰው ቅጣት፣ የማንም እጅ ሳይረዳት፣ በድንገት ከተገለበጠችው፣ ሰዶም ላይ ከደረሰው ቅጣት ይልቅ ታላቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ዋው። የማንም እጅ ሳይወድቅባት ድንገት ከተገለበጠች ከሰዶም ኃጢአት ይልቅ የወገኔ ሴት ልጅ ኃጢአት በዛች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በሕዝቤ ላይ የደረሰው ቅጣት የማንም እጅ ሳያርፍበት በቅጽበት ከተገለበጠችው ከሰዶም ቅጣት የበለጠ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ዋው። የማንም እጅ ሳይወድቅባት ድንገት ከተገለበጠች ከሰዶም ኃጢአት ይልቅ የወገኔ ሴት ልጅ ኃጢአት በዛች።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 4:6
14 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ዶ​ምና በገ​ሞራ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን አዘ​ነበ፤


እነ​ዚ​ያ​ንም ከተ​ሞች፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ፥ በከ​ተ​ሞ​ችም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ፥ የም​ድ​ሩ​ንም ቡቃያ ሁሉ ገለ​በጠ።


ሕዝቡ እንደ ካህኑ፥ ባሪ​ያ​ውም እንደ ጌታው ባሪ​ያ​ይ​ቱም እንደ እመ​ቤቷ፥ የሚ​ሸ​ጠ​ውም እን​ደ​ሚ​ገ​ዛው፥ ተበ​ዳ​ሪ​ውም እንደ አበ​ዳ​ሪው፥ ዕዳ ከፋ​ዩም እንደ ዕዳ አስ​ከ​ፋዩ ይሆ​ናል።


ያም ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው፥ ይቅ​ርም እንደ አላ​ላ​ቸው ከተ​ሞች ይሁን፥ በማ​ለ​ዳም ልቅ​ሶን፥ በቀ​ት​ርም ጩኸ​ትን ይስማ፤


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ነቢ​ያት ላይ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ በሐ​ሰ​ትም ይሄ​ዳሉ፤ ማንም ከክ​ፋቱ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን እጅ ያበ​ረ​ታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እንደ ገሞራ ሆኑ​ብኝ።


ጤት። በሰ​ይፍ የሞ​ቱት በራብ ከሞ​ቱት ይሻ​ላሉ፤ እነ​ዚህ የም​ድ​ርን ፍሬ አጥ​ተው ተወ​ግ​ተ​ውም ዐል​ፈ​ዋል።


በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።


በፍ​ርድ ቀን ሰዶም ከዚ​ያች ከተማ ይልቅ እን​ደ​ም​ት​ሻል ይቅ​ር​ታ​ንም እን​ደ​ም​ታ​ገኝ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


የጌ​ታ​ውን ፈቃድ ዐውቆ እንደ ፈቃዱ የማ​ይ​ሠ​ራና የማ​ያ​ዘ​ጋጅ የዚያ አገ​ል​ጋይ ቅጣቱ ብዙ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos