በዚህም ቤት ቢጸልዩና ቢለምኑህ፥ አንተ በሰማይ ስማ፤ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ምድር መልሳቸው።
ዘዳግም 30:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መበተንህም እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢሆን አምላክህ እግዚአብሔር ከዚያ ይሰበስብሃል፤ ከዚያም ያመጣሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ብትጋዝ እንኳ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ከዚያ ይሰበስብሃል፤ መልሶም ያመጣሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈለስክበት ስፍራ ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ቢሆን እንኳ፥ ጌታ እግዚአብሔር ከዚያ ይሰበስብሃል፤ ከዚያም መልሶ ያመጣሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ምድር ዳርቻ ተበታትነህ የምትኖር ብትሆን እንኳ አምላክህ እግዚአብሔር በአንድነት በመሰብሰብ መልሶ ያመጣሃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎችህም እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ፈልሰው እንደ ሆነ አምላክህ እግዚአብሔር ከዚያ ይሰበስብሃል፥ ከዚያም ያመጣሃል። |
በዚህም ቤት ቢጸልዩና ቢለምኑህ፥ አንተ በሰማይ ስማ፤ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ምድር መልሳቸው።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ቸርና መሓሪ ነውና፥ ወደ እርሱም ብንመለስ ፊቱን ከእኛ አያዞርምና ወደ እግዚአብሔር ብትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ በማረኩአቸው ፊት ምሕረትን ያገኛሉ፤ ደግሞም ወደዚህች ምድር ይመልሳቸዋል።”
ወደ እኔ ብትመለሱ ግን፥ ትእዛዜንም ብትጠብቁ፥ ብታደርጓትም ምንም ከእናንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢበተኑ፥ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስሜም ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥራል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ።
እነሆ፥ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል፥ “ለጽዮን ልጅ፦ እነሆ፥ መድኀኒትሽ ይመጣል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር ሥራውም በፊቱ አለ በሉአት።”
እነሆ፥ ከሰሜን ሀገር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ ለበዓለ ፋሲካ እሰበስባቸዋለሁ፤ ብዙ አሕዛብም ይወለዳሉ፤ ወደዚህም ይመለሳሉ።
ከአሕዛብም መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየሀገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም እመልሳችኋለሁ።
እግዚአብሔርም ከምድር ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ወደ አሉ አሕዛብ ሁሉ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተና አባቶችህ ያላወቃችኋቸውን ሌሎችን አማልክት፥ እንጨትንና ድንጋይን ታመልካለህ።