የምናሴም የነገድ እኩሌታ ልጆች፤ ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንና እስከ ሳኔር እስከ አርሞንኤም ተራራ እስከ ሊባኖስ ድረስ ተቀመጡ፤ እነርሱም በዙ።
ዘዳግም 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊኒቃውያን ኤርሞንን “ሳኒዮር” ብለው ይጠሩታል፤ አሞሬዎናውያንም ሳኔር ብለው ይጠሩታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አርሞንዔምን፣ ሲዶናውያን ሢርዮን ብለው ሲጠሩት፣ አሞራውያን ግን ሳኔር ይሉታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሔርሞንን ተራራ ሲዶናውያን ሢርዮን ብለው ሲጠሩት፥ አሞራውያን “ሠኒር” ብለው ሰይመውታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሔርሞንን ተራራ ሲዶናውያን ሢርዮን ብለው ሲጠሩት፥ አሞራውያን ‘ሠኒር’ ብለው ሰይመውታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲዶናውያን አርሞንዔምን ሢርዮን ብለው ይጠሩታል፥ አሞራውውያንም ሳኔር ብለው ይጠሩታል። |
የምናሴም የነገድ እኩሌታ ልጆች፤ ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንና እስከ ሳኔር እስከ አርሞንኤም ተራራ እስከ ሊባኖስ ድረስ ተቀመጡ፤ እነርሱም በዙ።
ሙሽሪት ሆይ፥ ከሊባኖስ ነዪ፤ ከሊባኖስ ነዪ፤ ከሃይማኖት ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥ ከአንበሶች ጕድጓድ፥ ከነብሮችም ተራራ ተመልከቺ።
እስከ ሴይርም ከሚያወጣው ከኤኬል ተራራ ጀምሮ ከአርሞንዔም ተራራ በታች እስከ ሊባኖስ ሜዳና እስከ በላጋድ ድረስ፤ ንጉሦቻቸውን ሁሉ ይዞ መታቸው፤ ገደላቸውም።