Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 27:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሳን​ቃ​ዎ​ች​ሽን ሁሉ ከሳ​ኔር ጥድ ሠር​ተ​ዋል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ሽ​ንም ይሠ​ሩ​ልሽ ዘንድ ከሊ​ባ​ኖስ ዝግ​ባን ወስ​ደ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሳንቃዎችሽን ሁሉ፣ ከሳኔር በመጣ ጥድ ሠሩ፤ ደቀልንም ይሠሩልሽ ዘንድ፤ ከሊባኖስ ዝግባ አመጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሳንቃዎችሽን ሁሉ ከሴኒር በመጣ ጥድ ሠሩ፤ ደቀልንም ሊሰሩልሽ ከሊባኖስ ዝግባ ወሰዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሳንቃሽ የተሠራው ከሔርሞን ተራራ በተገኘ ጥድ ነው፤ ምሰሶዎችሽ የተሠሩት በሊባኖስ ዛፍ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሳንቃዎችሽን ሁሉ ከሳኔር ጥድ ሠርተዋል፥ ደቀልንም ይሠሩልሽ ዘንድ ከሊባኖስ ዝግባ ወስደዋል።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 27:5
11 Referencias Cruzadas  

የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በዘ​መኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎ​ሞን በአ​ባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመ​ሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ወደ ሰሎ​ሞን ላከ።


አሁ​ንም ከወ​ገኔ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያን እን​ጨት መቍ​ረጥ የሚ​ያ​ውቅ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ለ​ህና የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ ይቈ​ር​ጡ​ልኝ ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን እዘዝ፤ አገ​ል​ጋ​ዮቼም ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ይሁኑ፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም ዋጋ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ሁሉ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


የም​ና​ሴም የነ​ገድ እኩ​ሌታ ልጆች፤ ከባ​ሳን ጀምሮ እስከ በኣ​ል​አ​ር​ሞ​ንና እስከ ሳኔር እስከ አር​ሞ​ን​ኤም ተራራ እስከ ሊባ​ኖስ ድረስ ተቀ​መጡ፤ እነ​ር​ሱም በዙ።


አሁ​ንም በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስና በብ​ረት፥ በሐ​ም​ራ​ዊና በቀይ፥ በሰ​ማ​ያ​ዊም ግምጃ መለ​በጥ የሚ​ች​ልና፥ አባቴ ዳዊት ካዘ​ጋ​ጃ​ቸው በእኔ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ካሉት ብል​ሃ​ተ​ኞች ጋር ቅርጽ ማው​ጣት የሚ​ያ​ውቅ ብል​ሃ​ተኛ ሰውን ላክ​ልኝ።


በም​ድር ላይ ራብን አመጣ፥ የእ​ህ​ልን ኀይል ሁሉ አጠፋ።


መቅ​ሠ​ፍቱ ከቍ​ጣው ነውና፥ መዳ​ንም ከፈ​ቃዱ ነውና፤ ማታ ልቅሶ ይሰ​ማል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆ​ናል።


ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ራስ ከሳ​ኔ​ርና ከኤ​ር​ሞን ራስ፥ ከአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ፥ ከነ​ብ​ሮ​ችም ተራራ ተመ​ል​ከቺ።


የሊ​ባ​ኖስ ዛፎች፦ አንተ ከተ​ዋ​ረ​ድህ ጀምሮ ማንም ይቈ​ር​ጠን ዘንድ አል​ወ​ጣ​ብ​ንም ብለው በአ​ንተ ደስ አላ​ቸው።


ዳር​ቻሽ በባ​ሕር ውስጥ ነው፤ ልጆ​ች​ሽም ውበ​ት​ሽን ፈጽ​መ​ዋል።


ፊኒ​ቃ​ው​ያን ኤር​ሞ​ንን “ሳኒ​ዮር” ብለው ይጠ​ሩ​ታል፤ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ሳኔር ብለው ይጠ​ሩ​ታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos