በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ ሀገር፥ በጋድ ሀገር፥ የአዴ ልጅ ጌቤር ነበረ፤ በይሁዳም ምድር ላይ እርሱ ብቻውን ሹም ነበረ።
ዘዳግም 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በዚያም ዘመን ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ኤርሞን ድረስ ምድሪቱን በዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩ ከሁለቱ ከአሞሬዎን ነገሥታት እጅ ወሰድን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በዚያ ጊዜ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሚገኘውን፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ ያለውን ግዛት፣ ከእነዚህ ከሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ላይ ወሰድንባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩት ሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት እጅ፥ ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ሔርሞን ተራራ ድረስ፥ ምድሪቱን ወሰድን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያን ጊዜ ከእነዚህ ከሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት በዮርዳኖስ ምሥራቅ፥ ከአርኖን ወንዝ እስከ ሔርሞን ተራራ ያለውን ምድር ሁሉ ያዝን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዘመን ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ ምድሪቱን በዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩ ከሁለቱ ከአሞራውያን ነገሥታት እጅ ወሰድን፤ |
በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ ሀገር፥ በጋድ ሀገር፥ የአዴ ልጅ ጌቤር ነበረ፤ በይሁዳም ምድር ላይ እርሱ ብቻውን ሹም ነበረ።
የምናሴም የነገድ እኩሌታ ልጆች፤ ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንና እስከ ሳኔር እስከ አርሞንኤም ተራራ እስከ ሊባኖስ ድረስ ተቀመጡ፤ እነርሱም በዙ።
የእርሱንና የባሳንን ንጉሥ፥ የዐግን ምድር፥ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩትን የሁለቱን የአሞሬዎንን ነገሥታት ምድር ወሰዱ።
የእስራኤልም ልጆች የመቱአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ በኩል ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን ሀገራቸውን የወረሱአቸው የምድር ነገሥት እነዚህ ናቸው፤
የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ ሰጣቸው ከእርሱ ከምናሴ ጋር የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀበሉ።