ሕዝቅያስም በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጣ፤ ወሰዳቸውም።
ዘዳግም 28:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሀገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ፥ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ሁሉ ያጠፋሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ፥ በደጆች ሁሉ ያስጨንቅሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትታመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከብባል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወርራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትተማመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪማረኩ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከባል፤ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር የሚገኙትን መኖሪያ ከተሞችህን ሁሉ ይከባሉ፤ አንተ የምትተማመንባቸውን ከፍተኞች የሆኑ ቅጽሮች ያሉአቸውን ምሽጎችህን ሁሉ ይደመስሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ደጆች ሁሉ ከብበው ያስጭንቁሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ በደጆች ሁሉ ከብበው ያስጨንቁሃል። |
ሕዝቅያስም በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጣ፤ ወሰዳቸውም።
ልጄንም ቀቅለን በላነው፤ በማግሥቱም፦ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው” ብላ መለሰችለት።
ምድራችሁ ባድማ ናት፤ ከተሞቻችሁ በእሳት ተቃጠሉ፤ እርሻችሁንም በፊታችሁ ባዕዳን ይበሉታል፤ ጠላትም ያጠፋዋል፤ ባድማም ያደርገዋል።
እግዚአብሔር፥ “ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም፤” ብሎ በጌትነቱና በክንዱ ኀይል ምሎአል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ በምድሪቱ የሚኖሩትን በመከራ አሰናክላቸዋለሁ፤ መቅሠፍትሽም እንዲያገኛቸው አስጨንቃቸዋለሁ።
ቤት። እግዚአብሔር የያዕቆብን መልካም ነገር ሁሉ አሰጠመ፤ አልራራምም፤ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አንባዎች አፈረሰ፤ ወደ ምድርም አወረዳቸው፤ መንግሥቷንና ግዛቷንም አረከሰ።
የቃል ኪዳኔንም በቀል ይበቀልባችሁ ዘንድ ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተማችሁም ትሸሻላችሁ፤ ቸነፈርንም እሰድድባችኋለሁ። በጠላቶቻችሁም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ፤
እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ለአሕዛብ ሁሉ የመንገድገድ ዋንጫ አደርጋታለሁ፣ ደግሞም ኢየሩሳሌም ስትከበብ በይሁዳ ላይ እንዲሁ ይሆናል።
አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ፣ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ፣ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም።
እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬ፥ የምድርህንም ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ እህልህን፥ ወይንህንም፥ ዘይትህንም፥ የላምህንና የበግህንም መንጋ አይተውልህም።