እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
ዘዳግም 28:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት፥ ብታደርጋትም፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም። ዛሬ የምሰጥህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ብትጠብቅ፣ መቼውንም ቢሆን በላይ እንጂ ፈጽሞ በታች አትሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም። ዛሬ የምሰጥህን የጌታ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትታዘዝ በጥንቃቄም ብትጠብቅ ሁልጊዜም በላይ እንጂ እታች አትሆንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክህ እግዚአብሔር በብዙ ሕዝቦች መካከል እንደ ራስ መሪ ያደርግሃል እንጂ እንደ ጅራት ወደ ኋላ እንድትቀር አያደርግህም፤ ዛሬ እኔ የምሰጥህን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በታማኝነት ብትፈጽም ምንም ዐይነት ውድቀት ሳይደርስብህ ወደፊት ትገሠግሣለህ እንጂ ወደ ኋላ አትቀርም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም። |
እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የያዕቆብ ቤት ሆይ! ደስ ይበላችሁ፤ በአሕዛብም አለቆች ላይ እልል በሉ፤ አውሩ፤ አመስግኑም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን የእስራኤልን ቅሬታ አድኖአል በሉ።
አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ ይባርክሃል፤ ለብዙ አሕዛብም ብዙ ታበድራለህ፤ አንተ ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብንም ትገዛለህ፤ አንተን ግን አይገዙህም።
ከአሕዛብ ሁሉ በላይ ትሆን ዘንድ፥ እርሱም እንደ ተናገረ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ታላቅ ስምን፥ ምስጋናና ክብርንም አደረገልህ።”
“እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽመህ ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ፥ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።
ነገር ግን ምናልባት የመጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳልኖርም ቢሆን በወንጌል ሃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስና በአንድ አካል ጸንታችሁ እንደምትኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራችሁ ለክርስቶስ ትምህርት እንደሚገባ ይሁን።