ዘዳግም 27:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተገለጠ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድንጋዮቹ ላይ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርገህ ጻፍባቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ ግልጽ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነዚያም ድንጋዮች ላይ የእግዚአብሔርን ሕግጋት ሁሉ በግልጥ እንዲነበቡ አድርገህ ጻፍ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተገለጠ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ። |
“ዛሬስ በምሳሌ ነገርኋችሁ፤ ነገር ግን የአብን ነገር ገልጬ እነግራችኋለሁ እንጂ ለእናንተ በምሳሌ የማልናገርበት ጊዜ ይመጣል።
ለአምላክህ ለእግዚአብሔርም የደኅንነት መሥዋዕት ሠዋበት፤ በዚያም ብላ፤ ጥገብም፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ።
ሙሴና ሌዋውያን ካህናት ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ፥ “እስራኤል ሆይ፥ ዝም ብለህ አድምጥ፤ ዛሬ የአምላክህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነሃል።
የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዘ፥ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፥ መሠዊያው ካልተወቀረና ብረት ካልነካው ድንጋይ ነበረ፤ በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ፤ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዋ።