ቤቱም በተሠራ ጊዜ ፈጽመው በተወቀሩ ድንጋዮች ተሠራ፤ ሲሠሩትም መራጃና መጥረቢያ፥ የብረትም ዕቃ ሁሉ በቤቱ ውስጥ አልተሰማም።
ዘዳግም 27:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካልተጠረበም ድንጋይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ፤ ለአምላክህም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብበት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአምላክህን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥራ፤ በላዩም ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርብበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካልተጠረበም ድንጋይ የጌታን የእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ፥ ለጌታ እግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር ለአምላክህ የምትሠራው ማናቸውም መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ መሆን አለበት፤ በዚያም የሚቃጠል መሥዋዕትህን አቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካልተጠረበም ድንጋይ የአምላክህን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ሥራ፤ ለአምላክም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብበት፤ |
ቤቱም በተሠራ ጊዜ ፈጽመው በተወቀሩ ድንጋዮች ተሠራ፤ ሲሠሩትም መራጃና መጥረቢያ፥ የብረትም ዕቃ ሁሉ በቤቱ ውስጥ አልተሰማም።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
ለአምላክህ ለእግዚአብሔርም የደኅንነት መሥዋዕት ሠዋበት፤ በዚያም ብላ፤ ጥገብም፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ።