ዘዳግም 27:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዕውሩን ከመንገድ ፈቀቅ የሚያደርግ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዐይነ ስውሩን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ፣ የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “‘ዐይነ ስውሩን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ፥ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ዕውርን ወደተሳሳተ አቅጣጫ የሚመራ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕውሩን ከመንገድ ፈቀቅ የሚያደርግ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። |
ሁሉም ዕውራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕውቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፤ በመኝታቸውም ሕልምን ያልማሉ፤ ማንቀላፋትንም ይወድዳሉ።
ደንቆሮውን አትስደብ፤ በዕውርም ፊት ዕንቅፋት አታድርግ፤ ነገር ግን አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።
ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።