ዘዳግም 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከጌታዉ ኰብልሎ ወደ አንተ የተጠጋውን ባሪያ ለጌታው አሳልፈህ አትስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ባሪያ ከአሳዳሪው ኰብልሎ ወደ አንተ ቢመጣ፣ ለአሳዳሪው አሳልፈህ አትስጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከጌታው ኮብልሎ ወደ አንተ የመጣውን ባርያ ለጌታው አሳልፈህ አትስጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ባሪያ ከጌታው በመኰብለል ወደ አንተ መጥቶ ቢጠጋ፥ ለጌታው አሳልፈህ አትስጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጌታው ኮብልሎ ወደ አንተ የመጣውን ባሪያ ለጌታው አሳልፈህ አትስጥ። |
የእግዚአብሔር ስም ለእናንተ ታላቅ ነው፤ ሀገራችሁም የሰፉ ወንዞችና ታላቅ የመስኖ ስፍራ ይሆናል፤ በዚህች መንገድ አትሄድም፤ መርከቦችም አይሄዱም።
የሸሹትንም ለማጥፋት በመተላለፊያ መንገዳቸው ትቆም ዘንድ፥ ድል በተነሡበትም ቀን ከእርሱ ያመለጡትን ለማስጨነቅ ትከብባቸው ዘንድ ባልተገባህ ነበር።
ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፣ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለምን ዝም ትላለህ?
አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።
ዳዊትም፥ “ወደ እነዚያ ሠራዊት ልትመራኝ ትወድዳለህን?” አለው፥ እርሱም፥ “እንዳትገድለኝ፥ ለጌታዬም እጅ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ በአምላክ ማልልኝ፤ እኔም ወደ እነዚያ ሠራዊት እመራሃለሁ” አለው።