ዘዳግም 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሐፍቱም ደግሞ ጨምረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድንጉጥ ሰው ቢሆን የወንድሞቹን ልብ እንደ እርሱ እንዳያስፈራ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ ብለው ለሕዝቡ ይናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አለቆቹ፣ “የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞቹም ልብ እንዳይባባ ወደ ቤቱ ይመለስ” በማለት ጨምረው ይናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከዚያም አለቆቹ፥ ‘የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞቹም ልብ እንዳይባባ ወደ ቤቱ ይመለስ’ በማለት ጨምረው ይናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጦር መሪዎች በሌላም በኩል እንዲህ ብለው ይጠይቁ፥ ‘ወኔ የጐደለው ፈሪ ሰው በመካከላችሁ ይገኛልን? እንዲህ ያለ ሰው ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እንዲህ ያለ ሰው የሌሎችን ወኔ ያቀዘቅዛል፤’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹም ደግሞ ጨምረው፦ ማንም ፈሪና ድንጉጥ ሰው ቢሆን እርሱ ፈርቶ የወንድሞቹን ልብ ደግሞ እንዳያስፈራ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ ብለው ለሕዝቡ ይናገሩ። |
ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድሪቱንም አዩአት፤ እግዚአብሔርም ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ የእስራኤልን ልጆች ልብ መለሱ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ማንም ዕርፍ ይዞ እያረሰ ወደ ኋላው የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይሆንም” አለው።
ወዴት እንወጣለን? ሕዝቡ ታላቅና ብዙ ነው፤ ከእኛም ይጠነክራሉ፤ ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሸጉም፥ እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፤ የረዐይትንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አስፈሩት።’
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”
እግዚአብሔርም አሁን እንግዲህ፥ “የፈራ፥ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕዝቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፤ ዐሥርም ሺህ ቀሩ።