የእስራኤልም ልጆች፥ “በተራራው በኩል እናልፋለን፤ እኛም ከብቶቻችንም ከውኃህ ብንጠጣ ዋጋውን እንከፍላለን፤ ይህ ምንም አይደለም፤ በተራራው እንለፍ” አሉት።
ዘዳግም 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገንዘብ በመለኪያ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ለምትበሉት ምግብም ሆነ ለምትጠጡት ውሃ በጥሬ ብር ትከፍሏቸዋላችሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፥ ውኃም ደግሞ በገንዘብ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያስፈልጋችሁን ምግብና ውሃ በገንዘብ ግዙ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገንዘብ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ። |
የእስራኤልም ልጆች፥ “በተራራው በኩል እናልፋለን፤ እኛም ከብቶቻችንም ከውኃህ ብንጠጣ ዋጋውን እንከፍላለን፤ ይህ ምንም አይደለም፤ በተራራው እንለፍ” አሉት።
የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።
አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ ይህን ታላቅና የሚያስፈራ ምድረ በዳ እንዴት እንደ ዞርኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፤ ከተናገርኸው ሁሉ አንዳችም አላሳጣህም።